avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
20.11.2025 20:42
ከውጭ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን በልዩ ኢኮኖሚ ዞን ለማምረት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተይዞ የነበረው እቅድ የሶስት ወራት አፈጻጸም 53 በመቶ ብቻ መሆኑ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ።

በዘንድሮ በጀት ዓመት ሶስት ወራት በልዩ ኢኮኖሚ ዞን በተመረቱ ተኪ ምርቶች ማዳን የተቻለው የገንዘብ መጠን 211 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ተብሏል።

ይህ አሃዝ ይፋ የተደረገው፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ህዳር 11፤ 2018 በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው።

የፓርላማው የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጠራው በዚህ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሶስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን አቅርቧል።


የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት፤ በልዩ ኢኮኖሚ ዘርፍ ከሚመረቱ ተኪ ምርቶች በሩብ አመቱ ለማዳን ታቅዶ የነበረው 400 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች 1.035 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ተኪ ምርቶችን ማምረታቸውን አስታውቆ ነበር።

🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16746/

@EthiopiaInsiderNews
12
👍 2
😁 2
5 12.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram