በአፋር ክልል፣ መጋሌ ወረዳ ላይ ከደረሰው “ጥቃት” በኋላ ከቶንሳ ቀበሌ እና ከአጎራባች አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛት 18 ሺህ ገደማ መድረሱን እና 11 ሺህ ያህሉ እስካሁን ድረስ ድጋፍ እንዳላገኙ የአካባቢው ባለስልጣናት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
የክልሉን ወሰን ተሻግረው ወደ አካባቢው መግባታቸው የተነገረላቸው “የትግራይ ኃይሎች” አሁንም ስፍራውን ለቅቀው አለመውጣታቸውንም ገልጸዋል።
የአፋር ክልል መንግስት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ባወጣው መግለጫ “የህወሓት ቡድን” ሲል የጠራው አካል፤ በመጋሌ ወረዳ በሚገኘው ቶንሳ ቀበሌ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ስድስት መንደሮችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል ወንጅሎ ነበር።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከአንድ ቀን በኋላ ባወጣው መግለጫ፤ የትግራይ ክልል ኃይሎች “ወደ አፋር ክልል ዘልቀው ጥቃት ፈጽመዋል” መባሉን “መሰረተ ቢስ” ሲል ማስተባበሉ አይዘነጋም።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይበል እንጂ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት፤ ታጣቂዎቹ ጥቃት መፈጸማቸውን እና አሁንም ስፍራውን ለቅቀው አለመውጣታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
አንድ የቶንሳ ቀበሌ ኃላፊ “የትግራይ ኃይሎች” ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂዎች ከሁለት ሳምንት በፊት የያዟቸው ሚልኪ፣ ዋረዓ፣ ሚላ፣ ከረፈቱ፣ ካኦሶበራ እና ከረሙአጋ የተባሉ አካባቢዎች አሁንም በእነርሱ ቁጥጥር ስር መሆኑን ገልጸዋል።
ዋረዓ በተባለ ቦታ ላይ ከስምንት ልጆቻቸው ጋር ተፈናቅለው የሚገኙ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ ከትላንት በስቲያ እሁድ ወደ መኖሪያቸው አቅራቢያ ተጉዘው አሁንም ስፍራው “በትግራይ ኃይሎች” ቁጥጥር ስር እንደሆነ እንደተመለከቱ የዓይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16724/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram