በቀን በአማካይ አምስት የውጭ ሀገር ዜጎች የሆኑ ግለሰቦች፤ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ሲጠቀሙ እንደሚያዙ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።
ሀሰተኛ የቪ አይ ፒ መስተንግዶ ሰነድ በማሰራት ወደ ተቋሙ የሚገቡ ሰዎች እንዳሉም መስሪያ ቤቱ ዛሬ በተካሄደ የፓርላማ የቋሚ ኮሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አመልክቷል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን የሶስት ወራት የስራ አፈጻጸም ለመገምገም፤ ዛሬ ሰኞ ህዳር 8፤ 2018 ስብሰባ የጠራው የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።
ሪፖርቱን በንባብ ያቀረቡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፤ መስሪያ ቤታቸው በሩብ አመቱ 545,491 ፓስፓርት ለዜጎች መስጠቱን ገልጸዋል።
በዚሁ ጊዜ ውስጥ 860 ኢትዮጵያዊን እና የውጭ ዜጎች ሀሰተኛ የጉዞ ሰነድ በማቅረባቸው ተይዘው በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጋቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ሀሰተኛ የጉዞ ሰነድ ይዘው የሚገኙ ዜጎች በመስሪያ ቤቱ ስራ ላይ “ተጨማሪ ጫና” መፍጠራቸውን የጠቆሙት ሰላማዊት፤ ችግሩ “በየጊዜው እየጨመረ የመጣ” ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል።
በተቋሙ ሪፖርት መሰረት፤ በሩብ ዓመቱ ውስጥ የተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ሲጠቀሙ የተያዙ የውጭ ሀገር ዜጎች ብዛት 96 ነው።
በፓርላማው የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሳዲቅ አደም፤ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በተመለከተ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ አሁንም “በርካታ” “ያልተደረሰባቸው” የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዳሉ በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16712/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram