avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.11.2025 19:38
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታን፤ በቦታው ሆኖ መመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ በዛሬው ዕለት ወደ አካባቢው መላኩን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናገሩ።

በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ “በሙከራ ደረጃ ላይ” ያሉ ክትባቶች እና መድኃኒቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ስራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ይህን የገለጹት በወቅታዊ የጤና ጉዳይ ላይ ዛሬ ሰኞ ህዳር 8፤ 2018 በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር መቅደስ በዚሁ መግለጫቸው መስሪያ ቤታቸው ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ 17 ናሙናዎች ወስዶ ባደረገው ምርምራ፤ ሶስቱ በበሽታው መያዛቸው ማረጋገጡን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በጤና ተቋማት እና ከዚያ ውጭ ያሉ ንክኪ የነበራቸው 129 ሰዎች “ራሳቸውን ለይተው እንዲያስቀመጡ” መደረጉን እና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ የተያዘ ሰው በህክምና ቦታ ውስጥ እንደሌለ የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ በላብራቶሪ ምርመራ የተገኙ ምልክቶች ያለባቸው ናሙናዎች “እያሰባሰቡ” መሆኑን አክለዋል።

ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከማከናወን ይልቅ በዚያው በሽታው በተከሰተበት አካባቢ ለማካሄድ እንዲቻል፤ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ በዛሬው ዕለት ወደ ጂንካ ከተማ መላኩንም ዶ/ር መቅደስ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በ12 ሀገራት የተከሰተው የማርበርግ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ “እንዴት መጣ?” የሚለውን ምላሽ የሚሰጥ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ከትላንት በስቲያ ወደ ስፍራው መጓዙንም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኃይሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16702/

@EthiopiaInsiderNews
9
👍 3
7 8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram