avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
16.11.2025 20:36
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በሚዛን አማን ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበሩ 27 ደቡብ ሱዳናውያን ወጣቶች ተፈትተው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገለጸ።

አርብቶ አደሮቹ ወጣቶች በኢትዮጵያ መቼ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ባይገለጽም፤ የደቡብ ሱዳን መገናኛ ብዙኃን አንድ ዓመት ገደማ በእስር ሳይቆዩ እንዳልቀረ ዘግበዋል።

ወጣቶቹን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሂደት በስኬት መጠናቀቁ የተገለጸው፤ የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መንደይ ሰማያ ከኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ጋር በጉዳዩ ላይ ያደረጉትን የስልክ ውይይት በማስመልከት በዛሬው ዕለት በተሰራጨ መግለጫ ነው።

የደቡብ ሱዳን መንግስት 27 የታጠቁ አርብቶ አደሮች፤ በኢትዮጵያ በእስር ላይ እንደሚገኙ ያረጋገጠው ባለፈው መስከረም ወር አጋማሽ ነበር።

የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አፑክ አዩኤል ማየን በወቅቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ከምስራቅ ኢኳቶሪያ ግዛት 27 ወጣቶች “በድንገት” ሁለቱ ሀገራት የሚዋሰኑትን ዓለም አቀፍ ድንበር እንዳቋረጡ ተናግረው ነበር።

ከ1,100 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ድንበር እየተሻገሩ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች ጭምር በየጊዜው ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል።

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በተጨማሪ በጋምቤላ በኩል ድንበር የሚሻገሩ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች፤ ግድያ፣ የህጻናት አፈና እና የቀንድ ከብቶች ዝርፊያ እንደሚፈጽሙ ክልሉ በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎች ማስታወቁ አይዘነጋም።

🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16698/

@EthiopiaInsiderNews
8
👍 6
6 6.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram