ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የመማሪያ መጽሐፍት ህትመትን በውጭ ሀገር ለማከናወን ከ16 ቢሊዮን ብር (105 ሚሊዮን ዶላር) በላይ ወጪ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከቅደመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚውል 24.7 ሚሊዮን የመማሪያ መጽሐፍት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያሳተመ ቢሆንም፤ እስከ 40 ሚሊዮን የሚደርስ የመጽሐፍት ፍላጎት አሁንም አለመሟላቱን ገልጿል።
መስሪያ ቤቱ ትላንት አርብ ህዳር 5፤ 2018 ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የሩብ ዓመት የስራ ሪፖርት፤ በህትመት ላይ የሚገኙት መጽሐፍት የእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ እና የአካባቢ ሳይንስ የትምህርት አይነቶችን የያዙ እንደሆነ አመልክቷል።
ህትመታቸው “በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ይጠናቀቃል” ለተባሉት ለእነዚህ መጽሐፍት ማሳተሚያ፤ ሚኒስቴሩ ሶስት ቢሊዮን ብር (19.8 ሚሊዮን ዶላር) ወጪ ማድረጉም በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።
ሪፖርቱን ለፓርላማው የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት በሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ ገላዬ፤ መስሪያ ቤታቸው ባለፉት ዓመታት የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍትን በማሳተም እና ወደ ክልሎች ለማውረድ እና ለተማሪዎች “አንድ ለአንድ ለማድረስ” መቻሉን አስታውሰዋል።
ከቅደመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የመማሪያ መጻሐፍት የማሳተም “የክልሎች ስራ” መሆኑን የገለጹት አቶ እሸቱ፤ የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት ይህንኑ ስራ ደርቦ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ክልሎች በራሳቸው አቅም መጽሐፍ የሚያሳትሙበትን ሁኔታ “እየተነጋገርን ነው” ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለዋል።
🔴 ለዝርዝሩ
https://ethiopiainsider.com/2025/16689/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram