avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
14.11.2025 22:38
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ከ15 እስከ 20 በመቶ ያሉትን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲያልፉ ማድረግ የሚቻል ከሆነ “በጣም ትልቅ” ውጤት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

አንድም ተማሪ ለዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ካልቻሉ እና ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ያህሉ ተለይተው፤ “የክትትል” እና “እገዛ” ስራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመርላቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፤ የመስሪያ ቤታቸው የሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ አርብ ህዳር 5፤ 2018 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየተመዘገበ ያለው ይህን መሰሉ ውጤት፤ ባለፉት ዓመታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄዱ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ከፍተኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ነበር።

የዘንድሮው የፈተና ውጤትም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስራዎች በሚከታተለው በፓርላማው የሰው ሃብት ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥያቄ ተነስቶበታል።

በቋሚ ኮሚቴው የትምህርት ዘርፍ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ ጌጡ፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ለዩኒቨርሲቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ካለፈው ዓመት አንጻር መሻሻል የታየበት ቢሆንም አፈጻጸሙ “አሁንም ዝቅተኛ” መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ታደሰ ባለፈው ዓመት ተማሪዎቻቸውን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውንም በተጨማሪነት ጠቅሰዋል።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16677/

@EthiopiaInsiderNews
17
🙊 6
🥱 4
👎 2
👏 2
🔥 1
😭 1
5 8.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram