የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን፤ የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ECF) አራተኛ ዙር ግምገማ፤ በባለሙያዎች ደረጃ ከስምምነት ለመድረስ የሚያስችል “አዎንታዊ እርምጃ” ማሳየቱን አስታወቀ።
በአራተኛው ዙር ግምገማ ላይ የሚደረገው ውይይት በመጪዎቹ ሳምንታት እንደሚቀጥል የልዑካን ቡድኑ መሪ አልቫሮ ፒሪስ ገልጸዋል።
የአይ ኤም ኤፍ ልዑካን ቡድን ይህን የገለጸው፤ ከጥቅምት 20 እስከ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 4፤ 2018 በአዲስ አበባ ጉብኝት ካደረገ በኋላ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።
የልዑካን ቡድኑ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ጨምሮ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር “ውጤታማ ውይይቶች” ማድረጉን አስታውቋል።
ባለሙያዎቹ ከባንኮች እና የግል ኩባንያዎች ጋር ጭምር መገናኘታቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ውይይቶቹ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚበደርበት ስምምነት አፈጻጸምን የተመለከቱ ናቸው።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ይህንን የተራዘመ የብድር አቅርቦት ያጸደቀው በሐምሌ 2016 ዓ.ም ነው።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በባለሙያዎች ያደረጋቸው ሶስት ግምገማዎችን መሰረት በማድረግ፤ 851.7 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ መንግስት ለቅቋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16660/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram