avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
13.11.2025 22:13
በወር ወይም በተርም የሚያስከፍሉትን የትምህርት ክፍያ፤ የትምህርት ዘመኑ ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ከተማሪ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ጋር በመወያየት፣ በግልጽ በማያሳውቁ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ 500 ሺህ ብር ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ።

ትምህርት ቤቶች የክፍያ አፈጻጸሞችን በትምህርት ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እና ድህረ ገጾች ላይ በግልጽ ካላሳወቁ፤ 100 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም በረቂቅ መመሪያው ላይ ተደነግጓል።

“ነጻና የግዴታ ትምህርት አተገባበር” የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መመሪያ የተዘጋጀው በትምህርት ሚኒስቴር ነው።

የትምህርት ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ዛሬ ሐሙስ ህዳር 4፤ 2018 ዓ.ም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋ የተደረገው ይህ ረቂቅ መመሪያ፤ በስድስት ክፍሎች እና በ35 አንቀጾች የተከፋፈለ ነው።

በመመሪያው ከተካተቱ ክፍሎች አንዱ “የግል ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍያዎችን” የሚመለከት ነው።

በዚህ ክፍል የትምህርት ክፍያዎች ፍትሃዊነት እና ተመጣጣኝነት፣ የክፍያ አወሳሰን፣ የክፍያ ዘዴዎች፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲሁም የተከለከሉ ክፍያዎች ምንነትን የሚዘረዝሩ ድንጋጌዎች ተካትተዋል።

“ግልጽነትን” የሚመለከተው የመመሪያው ድንጋጌ፤ ሁለም የግል ትምህርት ቤቶች በወር ወይም በተርም የሚከፈለውን የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ እና መመዝገቢያ “በይፋ መግለጽ” እንዳለባቸው ያስቀምጣል። ትምህርት ቤቶቹ ይህን ማድረግ የሚጠበቅባቸው “የትምህርት ዘመኑ ከመጀመሩ” በፊት እንደሆነም በድንጋጌው ላይ ሰፍሯል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16656/

@EthiopiaInsiderNews
16
8 6.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram