avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
13.11.2025 19:52
የዓለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የሄሞራጂክ ፊቨር (hemorrhagic fever) በሽታ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ46 ሚሊዮን ብር ገደማ አፋጣኝ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ድርጅቱ ሀገሪቱ በሽታውን ለመቆጣጠር ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ የሚሰጡ 11 አባላት ያሉበት ቡድን ማሰማራቱንም ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አካል የሆነው ተቋም ይህን የገለጸው፤ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ መከሰቱን ይፋ ባደረገ በማግስቱ ነው።

በዚሁ በሽታ እስካሁን ስምንት ሰዎች መጠርጠራቸውን ያመለከተው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፤ የበሽታው “ምንነት” ገና “በመረጋገጥ ላይ ያለ” መሆኑን አስታውቆ ነበር። 
 
የዓለም ጤና ድርጅት በዛሬው መግለጫው፤ የበሽታውን ትክክለኛ መንስኤ ለመለየት በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላብራቶሪ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የተከሰተው በሽታ፤ እንደ ኢቦላ፣ ማርቡርግ፣ ክሪሚያን ኮንጎ ሄሞራጂክ ፊቨር እና ላሳ ፊቨር ያሉ ተላላፊዎች ምድብ ውስጥ የሚካተት እንደሆነ ድርጅቱ በመግለጫው አመልክቷል።

የእዚህ አይነት በሽታዎች የመጀመሪያ ምልክቶች፤ ትኩሳት፣ ድካም፣ መፍዘዝ፣ የጡንቻ ህመም እና የጥንካሬ ማጣት መሆናቸውን ድርጅቱ ዘርዝሯል።

🔴 ለሙሉ ዘገባው➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16650/

@EthiopiaInsiderNews
16
👍 3
19 7.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram