avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
12.11.2025 20:55
በዛሬው ዕለት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሹመታቸው የጸደቀላቸው አቶ ጥራቱ በየነ፤ በከተማይቱ ያሉ የሰላም እና ጸጥታ ተቋማትን “ማጠናከር” እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎች እና መሰረተ ልማትን “ማስፋፋት” የትኩረት አቅጣጫቸው እንደሆነ ገለጹ።

አዲሱ ከንቲባ ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት ስራዎችን የማከናወን ባህልን ወደ ሀዋሳ ከተማ በማምጣት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚፈልጉም አስታውቀዋል።

አቶ ጥራቱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት፤ ዛሬ ረቡዕ ህዳር 3፤ 2018 በተካሄደ የከተማይቱ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ነው።

የአዲሱ ከንቲባ ሹመት እንዲጸድቅ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት፤ የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ናቸው።

ምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ለመምራት በዕጩነት የቀረበሉትን የአቶ ጥራቱን ሹመት ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

አዲሱ ከንቲባ ሹመታቸው መጽደቁን ተከትሎ ለምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ንግግር፤ የሀዋሳ ከተማን በሀገር አቀፍ እና በአህጉር ደረጃ “ተመራጭ የመኖሪያ፣ የቱሪዝም እና የኮንፍረንስ ከተማ ለማድረግ” “ከፍ ያለ ራዕይ” መሰነቃቸውን ተናግረዋል።

🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16643/

@EthiopiaInsiderNews
13
👍 5
👎 1
1 7.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram