ስለመጪው ምርጫ ሂደትም ሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተመለከተ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰባት መሰረታዊ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ጠየቁ።
መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎቹን በማሟላት፤ ለሁሉም ወገኖች “ነጻ እና ፍትሃዊ የሆነ” የውድድር ምህዳር እንዲፈጥሩ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጠኙ ፓርቲዎች እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች አንድነት መድረክ (መድረክ) የተሰኘው የፓርቲዎች ስብስብ ጥሪውን ያቀረቡት “በኢትዮጵያ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መፍጠርን” በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ ህዳር 3፤ 2018 በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው።
ፓርቲዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ ለመጪው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እያደረገ ያለውን “እንቅስቃሴ” በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርጫ ቦርድ ሂደቱን እያከናወነ ያለው በህግ ከተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት አንጻር መሆኑን እንደሚገነዘቡም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል።
ሆኖም ቦርዱ የጀመረው እንቅስቃሴ ለምርጫ “አስቻይ ሁኔታዎች” መኖራቸው “ባልተረጋገጠበት” እየተደረጉ ያለ በመሆኑ፤ “ጥረቱ ሁሉ ትርጉም አልባ መሆኑን በግልጽ መናገር እንፈልጋለን” ሲሉም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አስፍረዋል።
ዘጠኙ ፓርቲዎች በዛሬው መግለጫቸው የ2018 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ባለፈው ጊዜያት ከተካሄዱት “የተለየ” እና “አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት” የሚያስችል እንዲሆን፤ ምቹ ሁኔታ መፍጠር “አማራጭ” ሳይሆን “ቅድመ ሁኔታ መሆኑን” አጽንኦት ሰጥተዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16637/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram