avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
08.11.2025 00:28
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰው አልባ አውሮፕላን “ድብደባ በመፈጸም” በትግራይ ሰራዊት አባላት እና በአካባቢው ባሉ በነዋሪዎች ላይ “ጉዳት አድርሷል” ሲል ወነጀለ።

ህወሓት በዛሬው ዕለት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ በጻፈው ደብዳቤ፤ “የድሮን ጥቃቱ” የፕሪቶሪያ ስምምነትን “በግልጽ የጣሰ ነው” ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫም ይህንኑ የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን ስምምነት “በግልጽ ወደ መጣስ ተሸጋግሯል” ሲል በደብዳቤው ላይ የጠቀሰውን አቋም አስተጋብቷል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናው ባለፈው ግንቦት ወር የተሰረዘው ህወሓት፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት ለመጣሱ ማሳያ ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች በመግለጫው ዘርዝሯል።

በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን “በማደራጀት” እና “በማስታጠቅ” የኢትዮጵያን መንግስት የከሰሰው ህወሓት፤ ይህን የሚያደርገው “ትግራይን የማፍረስ” ስትራቴጂውን ለማሳካት እና የክልሉ ህዝብ “እርስ በእርስ እንዲጠፋፋ” በማሰብ እንደሆነም ወንጅሏል።

እነዚህን ታጣቂዎች በመጠቀም “ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት”፤ የኢትዮጵያ መንግስት “ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለል ሰፊ የማደናገሪያ ስራ እየሰራ ነው” ሲል ህወሓት በመግለጫው ከስሷል።

ህወሓት በመግለጫው “በጥቂት ከዳተኞች የተታለሉ” እና “ሽፍቶች” ሲል የጠራቸው ታጣቂዎች፤ በቅርብ ጊዜ በራያ አዘቦ ወረዳ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው እንደነበር ጠቅሷል። ፓርቲው ለተመድ ዋና ጸሀፊ በጻፈው ደብዳቤም፤ “በፌደራል መንግስቱ ይደገፋሉ” ያላቸው ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፈጽመውታል ያለውን ድርጊት አንስቷል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16616/

@EthiopiaInsiderNews
23
😁 17
👍 7
😢 4
8 9.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram