avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.11.2025 21:05
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጎንደር ከተማ ያለውን እና የታደሰውን የፋሲል አብያተ መንግስት ግቢ በመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ የሚጠቁም ገለጻ አድርገዋል። በቅርቡ ከውጪ የመጡ ሰዎች ጎንደርን በጎበኙበት ወቅት “መደነቃቸውን” እና “መደማቸውን” የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቀጣይነት ያቀረቡላቸው ምክረ ሃሳብ ግን አሁን ባለው የጸጥታ ሁኔታ መተግበሩ ላይ ያላቸውን ጥያቄ አንስተዋል።

“ ‘ከዚህ እስከ ጎርጎራ ድረስ ያለው መንገድ በራሱ ቢጠገን፤ ተራራው እና ውበቱ አይጠገብም’ አሉኝ። ‘ራሱ መንገድ ላይ ያለው፤ ያልለማው ተራራ፤ ትልቅ ውበት፣ ትልቅ ጸጋ አለው’ አሉ። ነገር ግን ከጎንደር ጎርጎራ ለመሄድ ጎንደሬዎች በወታደር ተጠብቀው እንዴት ልማት ሊሰራ ይችላል?” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

አብይ በዚሁ ንግግራቸው “ባዕድ ሳይሆን ባለአገሮች፣ ባለቤቶች፤ ከአንድ ሰፈር አንድ ሰፈር ተንቀሳቅሰው የሀገራቸውን ልማት ማየት፣ ማገዝ እንዲችሉ ሰላም ያስፈልጋል” ሲሉም የአካባቢውን የደህንነት ሁኔታ አመላክተዋል። ከጎንደር አካባቢ የወጡ ታጣቂዎችን “ወንድሞቻችን” ሲሉ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጊዜ ሳያባክኑ፤ ተመልሰው በልማት እና በስራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ጎንደርን፣ ባህርዳርን ወይም አማራ ክልልን ከአማሮች በስተቀር ማንም አያዝበትም። እኛ እንደው ሲፈቀድልን እንደ ዕድል ወስደን ከማገዝ ባሻገር በዕለት ተዕለት ጉዳይ እና ስራዎች ውስጥ እጃችንን አናስገባም” ሲሉም ተደምጠዋል። “ይሄ ዕድል ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም” ሲሉ አጽንኦት የሰጡት አብይ፤ “ከማበላሸት” ይልቅ “በትብብር መንፈስ” ለመስራት “በጋራ መቆም” እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
23
🤣 13
👍 2
🤔 2
3 8.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram