avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.11.2025 14:24
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ክልል ኃይሎች “ወደ አፋር ክልል ዘልቀው ጥቃት ፈጽመዋል” መባሉን አስተባበለ።

የአፋር ክልል ይህንኑ በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ “መስረተ ቢስ” ሲል ያጣጣለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፤ በትግራይ በኩል የሚፈጠር “ሁከትም” ይሁን “አለመረጋጋት” እንዲኖር “በፍጹም እንደማይፈልግም” ገልጿል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን ያለው ትላንት ሐሙስ ጥቅምት 27፤ 2018 ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ ነው። ጊዜያዊ አስተዳደሩ በዚሁ መግለጫው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ ሂደቶችን የሚያውኩ” እና “የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የሚጎዱ” ያላቸውን “እንቅስቃሴዎች” እየተመለከተ መሆኑ አስፍሯል። 

የትግራይ ክልልን ሆን ተብሎ “ለመበጥበጥ” እና “እርስ በእርስ ለማዳማት”፤ በአፋር ክልል ታጣቂዎች “በማደራጀት፣ እንዲታጠቁ ምቹ ቦታ በመፍጠር፣ በመደገፍ እና ተልዕኮ በመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ ቆይቷል” ሲል ጊዜያዊ አስተዳደር ወንጅሏል። በአፋር ክልል “ሀራ መሬት” የሚል መጠሪያ በሰጡት ቦታ ላይ የሚገኙት እነዚሁ ታጣቂዎች ካለፈው ዓመት ወዲህ ተደጋጋሚ “ትንኮሳዎች” ሲፈጽሙ መቆየታቸውን መግለጫው ከስሷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለዚህ በማሳያነት የጠቀሰው በከነባ እና አብዓላ አቅጣጫ በዚህ ዓመት በታጣቂዎቹ ተፈጽመዋል ያላቸውን ትንኮሳዎች ነው። ታጣቂዎቹ በዚህ ሳምንትም፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በደቡብ ትግራይ ራያ አዘቦ እና ራያ ጨርጨር ከህዝብ እና ከባለሀብቱ ጋር የነበረውን “የልማት ውይይት” ለማደናቀፍ የሚያስችሉ ተግባራትን ሲፈጽሙ መቆየታቸውን በመግለጫው አንስቷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16604/

@EthiopiaInsiderNews
14
👍 8
👎 3
🤣 2
4 8.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram