avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
06.11.2025 18:17
በአፋር ክልል “የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረዋቸዋል” ከተባሉ እና ከአጎራባች አካባቢዎች ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

ከቀያቸው የተፈናቀሉት ነዋሪዎች፤ በአፋር ክልል፣ ዞን ሁለት፣ መጋሌ ወረዳ በሚገኘው በፋሮ ቀበሌ እና በአቅራቢያው በሚገኙ ቦታዎች መጠለላቸውንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል።

በመጋሌ ወረዳ በሚገኘው ቶንሳ ቀበሌ ላይ ትላንት ረቡዕ ጥቅምት 26፤ 2018 በህወሓት ቡድን ጥቃት መፈጸሙን የአፋር ክልል መንግስት ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር።

የክልሉ መንግስት በዚሁ መግለጫው፤ የህወሓት ቡድን በዚሁ ቀበሌ የሚገኙ ስድስት አካባቢዎችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል ወንጅሏል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በስልክ ያነጋገረቻቸው ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች ይህንኑ የክልሉን መረጃ አረጋግጠዋል። በአሁኑ ወቅት በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ያሉ ቦታዎች ሚልኪ፣ ዋረዓ፣ ሚላ፣ ከረፈቱ፣ ካኦሶበራ እና ከረሙአጋ የተባሉ አካባቢዎች መሆናቸውን እነዚሁ ነዋሪዎች አስረድተዋል።

የአፋር ክልል መንግስት በትላንቱ መግለጫው፤ ዋራዓ እና ሚልኪ በተባሉ ቦታዎች የህወሓት ቡድን በንጹሃን የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ “የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍቷል” ሲል ወንጅሎ ነበር።

የቶንሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አንድ የዓይን እማኝ፤ የትላንቱ የከባድ መሳሪያ ተኩሱ የቆየው ከአመሻሽ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ጀምሮ እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16591/

@EthiopiaInsiderNews
22
😁 5
🤬 3
🕊 1
😭 1
11 8.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram