avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
06.11.2025 01:17
የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ በመግባት ስድስት መንደሮችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል የክልሉ መንግስት ወነጀለ። የአፋር ክልል መንግስት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ “በአስቸኳይ ካልተቆጠበ”፤ ራሱን “ከውጫዊ ጥቃት” የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስጠንቅቋል።

የአፋር ክልል መንግስት ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው፤ ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ገደማ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አማካኝነት ባወጣው አጭር መግለጫ ነው። ክልሉ በዚሁ መግለጫው “ጠብ ጫሪ” እና “ከጥፋቱ የማይማረው” ሲል የጠራው የህወሓት ቡድን፤ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 26፤ 2018 ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ “የከባድ መሳሪያ” ተኩስ መክፈቱን አስታውቋል።

ተኩስ የተከፈተባቸው አካባቢዎች በአፋር ክልል፣ ዞን ሁለት፣ መጋሌ ወረዳ፣ ቶንሳ ቀበሌ የሚገኙ አካባቢዎች መሆናቸውንም ክልሉ ገልጿል። የህወሓት ቡድን የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ ጥቃት ፈጽሞባቸዋል የተባሉት አካባቢዎች፤ ዋራዓ እና ሚልኪ የሚል መጠሪያ ያላቸው ናቸው።

“የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንዲመለሱ ቢማጸኗቸውም፤ ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል” ሲል የአፋር ክልል በዚሁ መግለጫው ላይ ወንጅሏል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከትላንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር፤ “በከሃዲነት” እና “በወንጀለኛነት” የፈረጁትን የህወሓት ቡድን “ጉጅሌ” የሚል ስያሜ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16573/

@EthiopiaInsiderNews
😁 18
16
🕊 12
😢 3
👍 1
25 7.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram