የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሓት ከፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት በኋላ አድርጓቸዋል ያሏቸው “ትንኮሳዎች”፣ “እምቢ ባይነቶች”፣ “ስራዎች” እና “ሴራዎች”፤ “ወደ ጦርነት ለመግባት ከበቂ በላይ ናቸው” አሉ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ “ጉጅሌ” ሲሉ የጠሩት በህወሓት ውስጥ ያለ ኃይል “እስካልተነቀለ ድረስ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም” ሲሉም ተደምጠዋል።
ኤታማዦር ሹሙ ይህን ያሉት፤ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈጸመበት አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ ስነ ስርዓት ላይ ትላንት ሰኞ ጥቅምት 24፤ 2018 ባደረጉት ንግግር ነው።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከትላንቱ ንግግራቸው አብዛኛውን ቦታ የወሰደው፤ የሰሜን ዕዝ ጥቃት እንዴት እና በእነማን እንደተፈጸመ ያብራሩበት ነው።
“የዛሬ አምስት ዓመት የተፈጸመውን ጥቃት “ክህደት” እና “አስነዋሪ ታሪክ” ሲሉ የጠሩት ኤታማዦር ሹሙ፤ ስለ ድርጊቱ ሲነሳ እየተወራ ያለው ስለ ህወሓት እንጂ ስለ ትግራይ ህዝብ አለመሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ህወሓት ራሱም በሙሉ አይደለም። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ጅምላ ይሆኑና ሀገር የሚጎዳ ድምዳሜ ላይ ይደረሳል” ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ድርጊቱ “መካድ በለመደ” የተወሰነ የህወሓት ስብስብ (ጉጅሌ) የተፈጸመ ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ስብስቡ እነማንን እንዳካተተ ኤታማዦር ሹሙ በንግግራቸው በግልጽ ባያመለክቱም፤ ይህን መሰል ስራውን ከጀመረ “50 ዓመት” እንደሆነው በመጠቆም የህወሓት የምስረታ ጊዜን አጣቅሰዋል።
ኤታማዦር ሹሙ የተለያዩ ውንጀላዎች ያቀረቡበትን የህወሓት ስብስብ በተደጋጋሚ “በከሃዲነት” ሲፈርጁም ተደምጠዋል።
🔴ለዝርዝሩ፦
https://ethiopiainsider.com/2025/16564/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram