በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለው “መካረር” ዳግም ወደ ጦርነት ያመራል የሚል “ከፍተኛ ስጋት” እንዳለው የገለጸው ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፤ ጉዳዩ “በንግግር” እና “በድርድር” እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።
ድርጅቱ መንግስት በትግራይ ክልል ያሉትን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ተፈናቃዮች የመመለስ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።
ሀገር በቀል የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋሙ ይህን ያስታወቀው፤ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 24፤ 2018 አዲስ አበባ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ድርጅቱ የዛሬውን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው፤ ተቀማጭነታቸውን በውጭ ሀገራት ያደረጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ከሆነው “ትግራይ አካውንተብሊቲ ኮአሊሽን” (Tigray Accountability Coalition) ጋር በመተባበር መሆኑን ገልጿል።
ጋዜጣዊ መግለጫው የተዘጋጀው፤ በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመት ያህል የቆየው ጦርነት የተጀመረበት አምስተኛ ዓመት እንዲሁም የፕሪቶሪያ ስምምነት የተፈረመበትን ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መሆኑንም ድርጅቱ ጠቅሷል።
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት ያስከተለውን “በጣም ሰፊ የሰው እልቂት፣ የኢኮኖሚ ውድመት እንዲሁም ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ” በማስቆሙ በአዎንታ እንደሚመለከቱት የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋአለም በርሀ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አመልክተዋል።
🔴 ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16555/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram