ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጉዳይን በተመለከተ ለአሜሪካ፣ ለቻይና፣ ለሩሲያ እና ለበርካታ ሀገራት “እንዲያሸማግሏት“ እና “መፍትሔ እንዲያመጡ“ ጥያቄ ማቅረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
በቀይ ባህር ምክንያት “ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውጊያ ከተነሳ ግን ውጤቱ “ግልጽ” እንደሆነ እና ሀገሪቱን “ማንም እንደማይስቆማት” አስጠንቅቀዋል።
አብይ ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 18፤ 2018 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካል ተገኝተው፤ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከቀይ ባህር እና የባህር በር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የጀመሩት የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይን በማንሳት ነው።
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሚመለከት “ኢ-ርትዓዊ”፣ “ኢ-ፍትሃዊ” እና “የበደል የመጨረሻው በደል” የተፈጸመባት ሀገር መሆኗን አብይ በማብራሪያቸው ላይ ጠቁመዋል።
ይህን ጉዳይ ለመናገር ክልከላ ሊደርግባቸው እንደማይገባ ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢ-ፍትሃዊ እና ኢ-ርትዓዊ ውሳኔ ባለበት ሁኔታ “የተሟላ ሰላም ሊፈጠር” እንደማይችል አስገንዝበዋል።
“ጦርነት የለም ማለት የተኩስ ድምጽ አይሰማም ማለት አይደለም። እውነተኛ ፍትህ ካልተረጋገጠ በማንኛውም ሰዓት ጦርነት ሊፈጠር ይችላል” ሲሉም አብይ አክለዋል።
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ያላት ጥያቄ “ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልዕክዓ ምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ነው ብለን እናምናለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ጉዳይ ከውጊያ ይልቅ “በህጋዊ መንገድ” እና “በንግግር ሊፈታ ይችላል” የሚለውን አቋማቸውን በማብራሪያቸው ደጋግመው አንጸባርቀዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16532/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram