avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.10.2025 23:31
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚከታተልበት “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” (early warning system) ለመዘርጋት ጥናት እያካሄደ መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታወቁ።

ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ስጋቶች መንጸባረቃቸውን የገለጹት ዋና ሰብሳቢዋ፤ ሆኖም “ምርጫው ይራዘማል የሚል ነገር እንደሌለ” መታወቅ አለበት ብለዋል።

ይህንን ያሉት ቦርዱ በረቂቅ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃን የተወጣጡ ተሳታፊዎች ጋር በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 17፤ 2018 ምክክር ባደረገበት ወቅት ነው።

ግማሽ ቀን በፈጀው በዛሬው ምክክር፤ በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ እና ደህንነት ችግርን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮች ተሰንዝረዋል።

ይህንኑ ችግር ያነሱ አንድ የመድረኩ ተሳታፊ፤ የጸጥታ ስጋትን በተመለከተ በመንግስት በኩል “ከፍተኛ”፣ “መካከለኛ” እና “ዝቅተኛ” በማለት የተለዩ ቦታዎች ስለመኖራቸው ጠይቀዋል። እኚሁ ተሳታፊ ጥያቄውን ያቀረቡት “ጸጥታ እና ደህንነት ካልተረጋገጠ”፤ ማንም ወደ ቦታዎቹ ሄዶ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት አይችልም በሚል እሳቤ እንደሆነም አብራርተዋል።

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ፤ መስሪያ ቤታቸው የምርጫ ክልሎችን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ መረጃዎችን ከክልሎች እንደሚቀበል አስረድተዋል። በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የሚኖሩ የጸጥታ ሁኔታዎችን በተመለከተ ደግሞ ቦርዱ ሪፖርት የሚያገኝበትን ስርዓት ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16515/

@EthiopiaInsiderNews
😁 10
4
🥰 2
3 9.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram