avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
26.10.2025 20:20
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ በስቲያ ማክሰኞ ጥቅምት 18 በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ የፓርላማ አባላት ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ እስካለፈው ሰኞ ድረስ ጥያቄዎቻቸውን አስገብተው እንዲያጠናቅቁ የተነገራቸው ባለፈው ሳምንት እንደነበር ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው ማክሰኞ የሚገኙበት መደበኛ ስብሰባ፤ በዓመት ውስጥ በፓርላማ በመገኘት ለጥያቄዎች ምላሽ ከሚሰጡባቸው ሶስት ሁነቶች የመጀመሪያው ነው።

በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት የፌደራል መንግስትን ዕቅድ ካቀረቡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ በመገኘት ገለጻ ማድረግ እንዳለባቸው ይደነግጋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የፌደራል መንግስትን የዘንድሮ ዓመት ዕቅድ ለተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት ያቀረቡት፤ የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ መስከረም 26 ነበር። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዚህ ይፋዊ መክፈቻ በኋላ መደበኛ ስብሰባ ያካሄደው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ምክር ቤቱ የአምስተኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ከነገ በስቲያ ማክሰኞ ጥቅምት 18 እንደሚያካሄድ ለፓርላማ አባላት መረጃዎችን በሚያሰራጭበት የቴሌግራም ቻናሉ በትላንትናው ዕለት ቢያስታውቅም፤ አጀንዳውን ከመግለጽ መቆጠቡን ምንጮች ገልጸዋል።

ሆኖም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አንድ የፓርላማ አባል፤ በዚሁ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ማረጋገጣቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16510/

@EthiopiaInsiderNews
25
👎 7
👍 2
4 8.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram