avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
23.10.2025 14:20
የፍትሕ ሚኒስቴር በእስር የሚቆዩ ታራሚዎችን ቁጥር “ከፍተኛ በሆነ መንገድ” ለመቀነስ ያስችላል ያለውን “የአማራጭ ቅጣት ስርዓትን” ለመተግበር ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። የአዋጁ ረቂቅ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው፤ የሚኒስቴሩን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ እና የሩብ ዓመት ስራ አፈጻጸም በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው። የፊት ለፊት የግምገማ መድረኩን ያዘጋጀው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።

ትላንት ረቡዕ ጥቅምት 12 በተካሄደው በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ የቋሚ ኮሚቴው አባላት በርካታ ጥያቄዎችን አቅርበው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በቋሚ ኮሚቴ አባላት ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፤ ተጠሪነታቸው ለፍትሕ ሚኒስቴር የሆኑት የፌደራል ማረሚያ ቤቶችን የተመለከቱት ይገኙበታል።

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ፤ የማረሚያ ቤት ጉዳይ የፖሊሲ ጣልቃ ገብነት (intervention) የሚፈልግ እንደሆነ ለፓርላማ አባላቱ አስረድተዋል። “አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ በጣም በርካታ ታራሚ ነው ያለው። ይሄን ሁሉ ታራሚ ይዘን፣ ይሄን ሁሉ እየቀለብን፣ ህክምና እንዲህ እያልን መቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ አለ ብለን አናስብም” ሲሉ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፍ የማዘጋጀቱ ጉዳይ ለነገ የሚባል እንዳልሆነ አብራርተዋል።

በዚህ ረገድ ሚኒስትር መስሪያ ቤታቸው፤ “በርካታ ስራዎችን” ለማከናወን ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ለዚህ በማሳያነት በመጀመሪያ የጠቀሱት በጉዳዩ ላይ እየተከናወነ ያለውን ሀገር አቀፍ ጥናት ነው።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16487/

@EthiopiaInsiderNews
18
🤡 3
🥰 1
😁 1
🌚 1
8 9.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram