avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
22.10.2025 23:49
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3 ነው።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር ላይ ነበር። በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከ60 በላይ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች መሳተፋቸውን፤ በመድረኩ የታደሙ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የ7ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ አቅርቧል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የጊዜ ሰሌዳ፤ 37 ተግባራት የሚከናወኑባቸውን ጊዜያት በቀን እና በወራት ከፋፍሎ አስቀምጧል።

በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው፤ ከህዳር መጀመሪያ እስከ ወሩ አጋማሽ ድረስ በምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች የምዝገባ ጥሪ ለማድረግ ታቅዷል።

የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለህዝብ ይፋ ማድረግ፤ ህዳር 19 ተጀምሮ በጥር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ለማጠናቀቅ ታስቧል። ይህ መርሃ ግብር በሁለት ዙር የሚከናወን መሆኑ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ተመልክቷል።

በምርጫ የሚሳተፉ ዕጩዎች ምዝገባ እንዲከናወን የታቀደው ከታህሳስ መጀመሪያ እስከ ጥር መጀመሪያ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። የምረጡኝ ቅስቀሳ ከታህሳስ 10 እስከ ግንቦት 19 ድረስ እንዲከናወን ቦርዱ አቅዷል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16480/

@EthiopiaInsiderNews
18
😁 13
17 7.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram