avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
21.10.2025 21:49
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “ህገ ወጥ ስራዎችን” ያከናውናሉ ባላቸው የሃዋላ አስተላላፊዎች ላይ “የማያዳግም” “ሰፊ እርምጃ” ለመውሰድ መዘጋጀቱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ።

ባንኩ የሚወስደው እርምጃ “የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ህግን የጠበቀ” እንደሚሆን የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዢው፤ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና “አስፈላጊውን ጥንቃቄ” እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ዶ/ር እዮብ “የመጨረሻ” ያሉትን ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት፤ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ የሃዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያቀኑት፤ የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ ስብሰባዎችን ለመካፈል ነው።

የብሔራዊ ባንክ ትኩረት “በርካታ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማት ህጋዊ በሆነ መንገድ ሰርተው ዘላቂነት ያለው ቢዝነስ ውስጥ እንዲቆዩ ነው” ያሉት ዶ/ር እዮብ፤ ሆኖም የተወሰኑ ድርጅቶች “የአጭር ጊዜ ትርፍ” ለማግኘት “በህገ ወጥ ስራ” ላይ ከመሰማራት እንዳልተቆጠቡ አስረድተዋል።

“የterrorism financing ወይም money laundering የምንለው ላይ የተሰማሩ፤ የተወሰኑ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማት እንዳሉ ደርሰንበታል። እዚህ ላይ በጣም የተናበበ፣ የተቀናጀ ሰፊ እርምጃ ለመውሰድ ነው ያሰብነው። ይሄንን አስቀድመን በግልጽ ነግረናቸዋል” ብለዋል የብሔራዊ ባንክ ገዢው።

ብሔራዊ ባንክ በህገ ወጥ ተግባራት የተሰማሩ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በምርመራ እንደደረሰባቸው ሲያስታውቅ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም።

🔵ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16475/

@EthiopiaInsiderNews
17
😁 7
💔 2
💊 1
48 11.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram