በሶማሌ ክልል፣ ሽንሌ ከተማ ትላንት ሰኞ ጥቅምት 11፤ 2018 ለሊት በደረሰ የባቡር ግጭት እና የመገልበጥ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች ሞተው፤ በ29 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሽንሌ ወረዳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። በተገለበጠው ባቡር ስር ያሉ ሰዎች ለማውጣት ጥረት እየተደረገ በመሆኑ፤ የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሏል።
የትላንቱ የባቡር አደጋ የተከሰተው ከድሬዳዋ እስከ ደወሌ የባቡር አገልግሎት በሚሰጠው የህዝብ እና የጭነት ማጓጓዣ ላይ ነው። አደጋ የደረሰባቸው ባቡሮች እና ፉርጎዎች በድሬዳዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት ስር የሚተዳደሩ ናቸው።
ትላንት ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ገደማ አደጋ የደረሰበት ባቡር፤ መነሻውን ከደወሌ አድርጎ ወደ ድሬዳዋ ይጓዝ የነበረ መሆኑን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
ዘይት፣ ስኳር እና ዱቄት የተጫነባቸው የባቡሩ ሁለት ፎርጎዎች ተንሸራትተው ከመስመር በመውጣት፤ ከድሬዳዋ አቅራቢያ በምትገኘው በሽንሌ ከተማ ለአስቸኳይ ስራ ከቆመ ባቡር ጋር በመጋጨታቸው መገልበጣቸውን የዓይን እማኞቹ አስረድተዋል።
በግጭቱ እና ይህንን ተከትሎ በደረሰ የባቡር መገልበጥ በአስቸኳይ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች እና ከደወሌ ይመጣ በነበረው ባቡር ላይ የነበሩ መንገደኞች መሞታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
በትላንቱ አደጋ 15 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን እና በ29 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን የሽንሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጀብሪል ኡመር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቀዋል።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16466/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram