avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.10.2025 00:43
ምስላዊ መረጃ፦ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያን የያዘ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ በዓመት ሁለት ጊዜ ትንበያዎቹን ካወጣ በኋላ ያሉ የየሀገራቱን የኢኮኖሚ አፈጻጸም በመገምገም፤ አሃዞቹን የመከለስ አካሄድን ይከተላል።

አይ ኤም ኤፍ በፈረንጆቹ 2023 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.1 በመቶ ያድጋል ብሎ የተነበየ ቢሆንም፤ ከወራት በኋላ ባደረገው ክለሳ ትክክለኛው እድገት 7.2 በመቶ መሆኑን አስታውቋል። ሀገሪቱ በ2024 ይኖራታል ያለውን የ6.2 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያም እንደዚሁ ከግምገማው በኋላ ወደ 8.1 በመቶ ከፍ አድርጎታል።

የድርጅቱ የዘንድሮ እና የመጪው ዓመት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያዎች፤ ካለፈው ዓመታት ተመሳሳይ አሃዞች ጋር ሲነጻጸሩ ከፍ ብለዋል። አይ ኤም ኤፍ በመገባደድ ላይ በሚገኘው 2025 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደሚያድግ የሚጠብቀው በ7.2 በመቶ ነው። እድገቱ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ወደ 7.1 በመቶ ይቀንሳል ሲልም ተንብይዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
👍 9
👎 8
6
7 10.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram