ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ለመጠናቀቅ ሁለት ወራት ብቻ በቀሩት የዘንድሮው የፈረንጆቹ ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነበየ። ድርጅቱ ሀገሪቱ በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2026 ዓመት ይኖራታል በሚል ያስቀመጠው እድገት፤ ለዚህ ዓመት ከተነበየው በ0.1 በመቶ ያነሰ ነው።
መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው አይ ኤም ኤፍ ይህን ያስታወቀው፤ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 6፤ 2018 ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርቱ ነው። ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች የሚገኙ 45 ሀገራትን የኢኮኖሚ ሁኔታ የዳሰሰ ነው።
በዚሁ ቀጠና ያለው የኢኮኖሚ እድገት፤ በፈረንጆቹ 2025 ዓመት 4.1 በመቶ በሆነ የተረጋጋ ሁኔታ እንደሚቀጥል አመልክቷል። ይህ የኢኮኖሚ ትንበያ በመጪው የፈረንጆቹ ዓመት “በትንሹ ከፍ” እንደሚል የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ለዚህም እንደ ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ባሉ ሀገራት እየተተገበሩ ያሉ “የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጥረቶች” አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው አመልክቷል።
በመጪዎቹ ጊዜያት የነዳጅ ዋጋ ይበልጥ ይቀንሳል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ቡና እና ወርቅን የመሳሰሉ ዋነኛ ሸቀጦች ዋጋ ግን ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ከነበረውም ጊዜ በላይ እንደሚሆን ሪፖርቱ አትቷል። ይህ ሁኔታ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በተፈጥሮ ሀብት ላይ ለተመሰረቱ ሀገራት ጠቃሚ እንደሚሆን አይ ኤም ኤፍ አስታውቋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16442/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram