avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
15.10.2025 22:38
ምስላዊ መረጃ፦ በትግራይ ክልል ካሉ ስድስት ወረዳዎች ተፈናቅለው የነበሩ 62 ሺህ ገደማ ሰዎች ባለፈው መስከረም ወር ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን በኢትዮጵያ ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚከታተለው የተቋማት ስብስብ (cluster) ገልጿል። ተፈናቃዮቹ የተመለሱት ወደ ኢሮብ፣ ጎሎመኸዳ፣ ዛላምበሳ፣ እገላ፣ ማዕከላዊ አድያቦ እና ታህታይ አድያቦ ወረዳዎች ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስት ድርጅትን ኤጀንሲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የተካተቱበት ይኸው ስብስብ ትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 4፤ 2018 ባወጣው ሪፖርት፤ ከፍተኛ የተፈናቃይ ተመላሾች ቁጥር የተመዘገበው በታህታይ አድያቦ ወረዳ መሆኑን አስታውቋል። በመስከረም ወር ወደ ወረዳው የተመለሱ ሰዎች ብዛት 29,232 መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ከአስራ ሁለት ሺህ በላይ ቤተሰቦች ወደ እነዚህ ወረዳዎች መመለሳቸው “ተፈናቃዮች በራሳቸው ተደራጅተው የመመለስ” እንቅስቃሴን የሚያመለክት መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
9
😁 3
👍 1
10 8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram