avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
15.10.2025 13:02
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ አቅራቢያ ባለፈው መስከረም ወር ሁለት የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂ ቡድኖች ታፍነው መወሰዳቸውን አንድ ሪፖርት አመለከተ። በክልሉ ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው የመካነ ሰላም የተፈናቃዮች መጠለያ፤ በአካባቢው ባለው አስቸጋሪ የጸጥታ ሁኔታ እና ግጭት ምክንያት ለሰብአዊ እርዳታ አሁንም ተደራሽ አለመሆኑን ሪፖርቱ ገልጿል።

ሪፖርቱን ትላንት ጥቅምት 4 ያወጣው፤ በኢትዮጵያ ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚከታተለው ስብስብ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማትን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን፣ ለጋሾችን እና የመንግስት ተቋማትን ያካተተው ስብስብ በዚሁ ሪፖርቱ፤ በመስከረም ወር በተለያዩ አካባቢዎች የነበሩ ሁኔታዎችን ዳስሷል።

ወርሃዊው ሪፖርት በዳሰሳው ከሸፈናቸው አምስት ክልሎች መካከል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ውጊያ እየተካሄደበት የሚገኘው የአማራ ክልል ይገኝበታል። በክልሉ ያለው ግጭት በትራንስፖርት መዋቅሩ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደሩን ሪፖርቱ አመልክቷል። የጭነት መኪናዎችን እና የአገር አቋራጭ አውቶብሶችን የሚያሽከረክሩ ሹፌሮችን ኢላማ ያደረጉ እገታዎች እንደሚፈጸሙም ሪፖርቱ ጠቅሷል።

በመስከረም ወር በጎንደር ከተማ አቅራቢያ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂ ቡድኖች ታፍነው የተወሰዱ ሁለት የእርዳታ ሰራተኞች፤ በደባርቅ እና ጎንደር መካከል ባለው መንገድ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የደህንነት ችግር አጎልቶ ያሳየ መሆኑን ሪፖርቱ ገልጿል።

የደባርቅ ጎንደር መንገድ ለሰብአዊ እርዳታ እንቅስቃሴዎች እና ለሰላማዊ ሰዎች አሁንም “ከፍተኛ አደጋ” የደቀነ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16428/

@EthiopiaInsiderNews
7
😢 6
12 7.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram