ለሁለት ዓመት የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ (chief of staff) ሆነው ያገለገሉት አቶ ሳንዶካን ደበበ፤ በዛሬው ዕለት የማቋቋሚያ ደንቡ የጸደቀለትን የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ ተሾሙ። አቶ ሳንዶካን ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሹመት ሲያገኙ በአምስት ዓመት ውስጥ ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቶ ሳንዶካንን ከዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4፤ 2018 ጀምሮ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው መሾማቸውን ያስታወቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው። አቶ ሳንዶካን ይህንን መስሪያ ቤት እንዲመሩ ከመሾማቸው አስቀድሞ፤ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ላለፉት 14 ዓመታት ሰርተዋል።
በ2001 ዓ.ም. ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምግብ ሳይንስ እና በምርት አሰባሰብ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ሳንዶካን፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምግብ ሳይንስ እና ኒዩትሪሽን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ይዘዋል። ወጣቱ የመንግስት የስራ ኃላፊ የብዙዎቹን ትኩረት የሳቡት፤ ሌላኛዋን ወጣት ባለስልጣን ለሊሴ ነሜን በመተካት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን በሰኔ 2012 ዓ.ም. ሲሾሙ ነበር።
በኮርፖሬሽኑ ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ የቆዩት አቶ ሳንዶካን፤ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት በጥቅምት 2015 ዓ.ም ነበር። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአንድ ዓመት ብቻ በኃላፊነት የሰሩት አቶ ሳንዶካን፤ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው በጥቅምት 2016 ዓ.ም. ተሹመዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16410/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram