avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
14.10.2025 13:41
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4፤ 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብስባ፤ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን የሚያቋቁም ደንብ አጸደቀ። ደንቡ የጸደቀው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ “ለማቀድ እና ለመገንባት” የሚያስችል ሰነድ በተፈራረሙ በሁለት ሳምንት ገደማ ልዩነት ነው።

ዛሬ በጸደቀው ደንብ መሰረት የሚቋቋመው ኮሚሽን፤ ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች በተጣጣመ መልኩ “ለሰላማዊ መንገድ” ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት “የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት” እንደተጣለበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይልን ለኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለጤና አገልግሎት፣ ለሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ለመጠቀም እንዳቀደች ጽህፈት ቤት ዛሬው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በ30 ቢሊዮን ዶላር ሊገነባ ካቀዳቸው “ሜጋ ፕሮጀክቶች” መካከል የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ አንዱ መሆኑን ከሳምንት በፊት ገልጾ ነበር። ይህንን የመንግስት ዕቅድ መስከረም 22፤ 2018 በተከናወነ ስነ ስርዓት ላይ ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናቸው። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ባሰሙት ንግግር፤ የሜጋ ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ ተጠንተው፣ ዝግጅት ተደርጎባቸው እንዲሁም የሀብት ምንጫቸው ተለይቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል። የፕሮጀክቱ ግንባታም “ካለምንም ጥርጥር በሚቀጥሉት አምስት እና ስድስት ዓመታት” እንደሚፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ቃል ገብተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16391/

@EthiopiaInsiderNews
😁 9
7
👍 1
7 7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram