በአዲስ አበባ ከተማ በዚህ ዓመት የሚጀመር አዲስ ኮሪደር ልማት እንደማይኖር የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የከተማይቱ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት ከኮሪደር ልማት ጎን ለጎን ለመስራት ባለፈው ዓመት ከመረከቡ በፊት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በውጭ እርዳታ እና ዜጎች የተከናወነው ስራ “ሁለት ኪሎ ሜትር ብቻ” እንደነበር ከንቲባዋ ይፋ አድርገዋል።
አዳነች ይህን ይፋ ያደረጉት ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3፤ 2018 ዓ.ም በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።
“በዚህ ዓመት ኮሪደር ብለን፣ ለኮሪደር እንደ አዲስ የምንጀምረው አይኖረንም። ጥናት እናደርጋለን። ቤቶች እንገነባለን፣ በጥናታችን መሰረት ከህዝብ ጋር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ቦታዎች ያልናቸው ላይ ውይይቶች እናደርጋለን” ሲሉ ከንቲባ አዳነች ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም. “ትልቁ ትኩረት” የቤት ግንባታ እና የውሃ አቅርቦት መሆኑን ያመለከቱት ከንቲባዋ፤ ለዚህም የሚሆን በጀት የከተማይቱ ምክር ቤት ባለፈው መደበኛ ጉባኤው ማጽደቁን አስታውሰዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ባደረገው መደበኛ ጉባኤው ካጸደቀ በጀት ውስጥ ለቤቶች ልማት ዘርፍ የተመደበው 24.66 ቢሊዮን ብር ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ የዘንድሮ በጀት ከዘርፎቹ ሁሉ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የተመደበለት የመንገድ ልማት ዘርፍ ነው። ዘርፉ 31.49 ቢሊዮን ብር ተበጅቶለታል። የከተማይቱ አስተዳደር ዘንድሮ በሚገነባቸው መንገዶች “የኮሪደር ልማት ስታንዳርድን” እንደሚተገብር ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።
🔴 ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16377/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram