avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
12.10.2025 01:09
በስልጤ ዞን ከወረዳ እስከ ፓርላማ ገዢውን ፓርቲ ወክለው የተመረጡ ተወካዮች፤ በጥቂት ወራት ውስጥ እያንዳንዳቸው 10 ቤት ለህዝብ ካልገነቡ በመጪው ምርጫ የአካባቢው ሰው ድምጽ እንዳይሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ።

የፌደራል መንግስት 1.5 ሚሊዮን ቤቶች የግንባታ ዕቅድ፤ እንደ ስልጤ ዞን ባሉ አካባቢዎች በገጠር ኮሪደር ልማት የሚሰሩ ቤቶችን እንደሚያካትትም አብይ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ እና የቤት ግንባታ ያስተሳሰሩበትን አስተያየት የሰጡት፤ የዞኑን አመራሮች ጨምሮ ከከፍተኛ የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት ጋር “የገጠር ኮሪደር ስራዎችን” በተመለከተ ትላንት አርብ መስከረም 30፤ 2018 ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በከተሞች ከሚያከናውነው የኮሪደር ልማት በተጨማሪ በገጠርም ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት ልክ የዛሬ ዓመት ነበር።

አብይ በገጠር ኮሪደር የመኖሪያ ቤት እና ተያያዥ መሰረተ-ልማት የሚገነቡባቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ አራት ዞኖች ባለፈው ረቡዕ እና ትላንት አርብ ተዘዋውረው ጎብኘተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ፤ ሀላባ፣ ከምባታ፣ ሀዲያ እና ስልጤ ዞኖችን ያዳረሰ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ በጎበኟቸው ሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የተሰሩ ቤቶች ከመረቁ በኋላ፤ ሁለቱ ዞኖች እያንዳንዳቸው 100 ቤቶች እንዲሰሩ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህ ትዕዛዝ “በየዋህነት” እና “በስህተት” የተላለፈ እንደነበር በትላንቱ ውይይታቸው የጠቀሱት አብይ፤ “ካለማወቅ ነው ይቅርታ ይደረግልኝ” ሲሉ ተደምጠዋል።

🔴 ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16354/

@EthiopiaInsiderNews
🤣 31
24
🤔 4
👎 2
9 7.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram