avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
11.10.2025 19:16
በአዲስ አበባ ከተማ “የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለንግድ ስራ አውለዋል” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በሶስት ቀናት ገደብ ውስጥ እስከ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለሌላ አገልግሎት ለማዋል የሚያስችላቸውን የሊዝ ውል ለውጥ ለማድረግ ከመቶ ሺህዎች እስከ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ክፍያ መጠየቃቸውንም ገልጸዋል።

በመዲናይቱ በሚገኙት በአቃቂ ቃሊቲ፣ በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ ባለፉት ቀናት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች እንደደረሷቸው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጣለች።

በአንዳንዶቹ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የንግድ ቤቶች እና አገልግሎት መስጪያዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች መለጠፋቸውንም የየአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
   
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ዓለም ባንክ አዲሱ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ ከክፍለ ከተማ መምጣታቸውን የገለጹ ሰራተኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤውን ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ፤ ነዋሪዎቹ መሬት የወሰዱት ለመኖሪያ አገልግሎት ለመዋል እንደሆነ ይጠቅሳል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16343/

@EthiopiaInsiderNews
10
💔 3
👍 1
50 7.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram