avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
11.10.2025 15:51
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልሎች ባሉ መንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት “አደጋ ላይ መውደቁን” አስታወቀ።

በእነዚሁ ክልሎች በሚጣሉ ኬላዎች፣ የመንገድ መዘጋት እርምጃዎች፣ የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደቦች እና በመንገዶች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች “አሳሳቢ” ሆኖ እንዳገኘው ኢሰመኮ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው፤ “በግጭት ዐውድ” ውስጥ እና “ከግጭት ዐውድ ውጪ” ባሉ አካባቢዎች ያደረገውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ግኝት በተመለከተ ባወጣው ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 1 ባወጣው መግለጫ ነው። ኢሰመኮ ክትትል እና ምርመራውን ያከናወነው ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት መሆኑን አስታውቋል።

በአራት ክልሎች በተደረገው በዚህ ክትትል እና ምርመራ፤ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችን፣ የዓይን ምስክሮችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እንዲሁም የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላትን በማነጋገር “መረጃ እና ማስረጃዎችን” ማሰባሰቡን ኮሚሽኑ አመልክቷል። ኮሚሽኑ በመግለጫው “አሳሳቢ” ያላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንም ዘርዝሯል።

በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚጣሉ የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደቦች፣ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች እና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች “በመንገዶች ላይ በሚጣሉ ኬላዎች”፣ የመንገድ መዝጋት ትዕዛዞች፤ የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት “አደጋ ላይ መውደቁ” በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16324/

@EthiopiaInsiderNews
15
8 6.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram