avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
09.10.2025 21:07
ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መስራቾች አንዱ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ፤ ዓለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት (IPI) እና ዓለም አቀፍ ሚዲያ ሰፖርት (IMS) የተባሉ ተቋማት በትብብር ለሚሰጡት የዓለም ፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተመረጠ። የእዚህን ዓመት ሽልማት እንዲቀበሉ የተመረጡት ተስፋለምን ጨምሮ 7 ጋዜጠኞች እና አርታዒያን ናቸው።

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለሚዲያ ነጻነት ወይም ያልተገደበ የዜና እና የመረጃ ፍሰት በተለይ ግለሰባዊ ደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሆኖ ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ጋዜጠኞች የሚሰጥ ነው። ተስፋለም ለሽልማቱ የተመረጠው “ለገለልተኛ ጋዜጠኝነት ባለው የማይናወጥ ቁርጠኝነት” እንደሆነ ሸላሚዎቹ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 29 ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ጋዜጠኛው “ከባለስልጣናት ለሚሰነዘር ቀጥተኛ የበቀል እርምጃ” ዒላማ ከመሆኑ ባሻገር በሥራው ምክንያት “የግል ሕይወቱን በተደጋጋሚ ለአደጋ እንዳጋለጠ” ሸላሚዎቹ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። ከ1 ዓመት በላይ የሚረዝመውን ጨምሮ ለተደጋጋሚ የዘፈቀደ እስራት የተዳረገው ተስፋለም፤ “ከጊዜ ወደ ጊዜ ለነጻ ሚዲያ አስቸጋሪ በሆነ ምህዳር ውስጥ ለሕዝብ ለሚጠቅም ጋዜጠኝነት ቦታ ለመፍጠር ባለው ቁርጠኝነት” ተሰድዶ ከነበረበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን ተቋማቱ በመግለጫቸው አመልክተዋል። 

“ይህ ክብር ለእኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እና በስደት ላይ ለሚገኙ ብርቱ ጋዜጠኞች ጭምር ነው” ያለው ተስፋለም፤ ሽልማቱ “በየዕለቱ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ለሚውሉ፣ ለሚታሰሩ፣ ማስፈራራት፣ ወከባ፣ ዛቻ ለሚገጥማቸው፣ ለሚከሰሱ እና ጥቃት ለሚፈጸምባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ድፍረት እና ለሙያቸው ያላቸው ታማኝነት ምስክር” እንደሚሆን ገልጿል።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16310/

@EthiopiaInsiderNews
👏 24
12
👍 5
👎 2
😁 1
4 7.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram