ቪዲዮ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ24ኛው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት ዛሬ ረፋዱን ኬንያ መዲና ናይሮቢ ገብተዋል። ሃያ አንድ አባል ሀገራትን ያቀፈው ኮሜሳ በዚህ ዓመት ጉባኤው ትኩረት ያደረገው “ዲጂታይላዜሽን” ላይ ነው።
ዘርፉን “ለዘላቂ እና አካታች ዕድገት” ማዋል እንዴት እንደሚቻል በመከረው በዚህ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ አሳይታዋለች ያሉትን እመርታ ለተሰብሳቢው አብራርተዋል። በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት አገልግሎቶችን “ያለ እንቅፋት እና ቢሮክራሲ ለህዝብ ተደራሽ አድርገናል” ሲሉም ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ እየተተገበረ በሚገኘው የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም “ከ25 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ መሆኑንም” አንስተዋል። ይህን ፕሮጀክት በመንግስት እና በቢዝነሶች ላይ “እምነትን” ለማሳደር እና “ቅልጥፍናን” ለመጨመር “መሰረት የጣለ ነው” ሲሉ አሞካሽተውታል።
በሀገሪቱ ባለው የዲጂታል ክፍያ ስርዓት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ግብይቶች ባለፈው ዓመት መከናወኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በብሔራዊ የኮዲንግ ፕሮግራም ከ2.2 ሚሊዮን በላይ ወጣት ኢትዮጵያውያን የዕውቅና ማረጋገጫ ማግኘታቸውንም አመልክተዋል።
“ከዚህ ልምድ የተማርነው ቀላል እውነት፤ አፍሪካ በተሰጥኦ እና በዲጂታል መሰረቶች ላይ ኢንቬስት በምታደርግበት ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በራሷ አካሄድ መወዳደር እንደምትችል ነው። ቀጣይ እርምጃችን ሊሆን የሚገባው እነዚህን ሀገራዊ ጥረቶች ከቀጠናው ጋር ማገናኘት ነው” ሲሉም አብይ አሳስበዋል።
🔴 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ለመመልከት፦
https://youtu.be/5Lm0NC52mB8
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram