avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.10.2025 21:34
በኢትዮጵያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የሚፈስሰውን የአውሮፓ መዋዕለ ንዋይ ለማሳደግ ያለመ ኮንፍረንስ በፈረንሳይ ፓሪስ ሊካሄድ ነው። ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ከ100 በላይ የአውሮፓ ኩባንያዎች ተወካዮች ይታደማሉ ተብሏል።
 
በመጪው ጥቅምት 24፤ 2018 የሚካሄደውን ይህን ኮንፍረንስ በጋራ ያዘጋጁት የፈረንሳይ ቢዝነስ ኮንፌዴሬሽን (Medef) እና የአውሮፓ ኮሚሽን ናቸው። የፈረንሳይ ቢዝነስ ኮንፌዴሬሽን 173 ሺህ ኩባንያዎች አባል የሆኑበት እና በሀገሪቱ የሚገኙ ዋነኛ ቀጣሪዎችን በስሩ ያቀፈ ቁልፍ ተቋም ነው። 

ኮንፌዴሬሽኑ ለሚመለከታቸው አካላት በዛሬው ዕለት ባሰራጨው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በተመለከተችው የግብዣ ጥሪ፤ ኢትዮጵያን በሚመለከት በሚዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማት፣ የልማት ፋይናንስ ተቋማት እና የቢዝነስ ተወካዮች እንደሚሳተፉ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል በፓሪሱ ኮንፍረንስ ላይ ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው።

ለፓሪሱ ኮንፍረንስ ከተመረጡ ዘርፎች መካከል በቀዳሚነት የተቀመጡት ትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክስ እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ የሚያስገነባው አየር ማረፊያ በኮንፍረንሱ በዋነኛነት ከሚቀርቡ የኢንቨስትመንት አማራጮች አንዱ እንደሚሆን በግብዣ ሰነዱ ላይ ተመልክቷል። 

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16283/

@EthiopiaInsiderNews
19
😁 5
👏 2
5 7.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram