avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
04.07.2025 23:17
የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰረዙባቸው ተጨማሪ ምክንያቶችን የያዘ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ   

በግለሰቦች፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል “ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል” ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ።

ቦርዱ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን “ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደናቀፈ” የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰድ ስልጣንም በአዋጅ ማሻሻያው ተሰጥቶታል። 

ላለፉት አምስት ዓመታት በስራ ላይ የቆየውን “የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ” ያሻሻለው የህግ ረቂቅ ለፓርላማ የቀረበው፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አርብ ሰኔ 27፤ 2017 ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ላይ ነው።

ያለምንም ተቃውሞ እና ድምጸ ተዐቅቦ ለቋሚ ኮሚቴ የተመራው ይህ የአዋጅ ማሻሻያ ከተዘጋጀባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስፈጸመው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት የተስተዋሉ “የህግ ክፍተቶች” እንደሆነ የህግ ረቂቁን ለማብራራት በቀረበ ሰነድ ላይ ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ መልኩ “የህግ ክፍተቶች” በፖለቲካ ፓርቲ አስተዳደር ስራዎች ላይ እንዳሉ ያመለከተው ሰነዱ፤ ይህንኑ ለመቅረፍ የአዋጅ ማሻሻያው መዘጋጀቱን ይገልጻል። 

ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው የህግ ረቂቅ ካካተታቸው ማሻሻያዎች መካከል፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “መታገድ፣ መሰረዝ እና መፍረስ” የሚመለከተው ክፍል ይገኝበታል።

🔴 ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16239/

@EthiopiaInsiderNews
19
😁 8
👏 1
12 11.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram