በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው “በፍጥነት” ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ
የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26፤ 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በሁለት ክፍል የቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ቅድሚያውን እና ሰፊውን ጊዜ የሰጠው፤ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች ነበር።
ሶስት ሰዓት ገደማ ከፈጀው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ውስጥ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ የተመደበለት አንድ ሰዓት ያልሞላ ጊዜ ነበር። በዚህኛው የማብራሪያ ክፍል ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ ትግራይ እና ኤርትራን የተመለከቱት ይገኙበታል።
“የትግራይ ህዝብ መቶ ፐርሰንት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት አብይ፤ ከህዝብ ፍላጎት እና አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። “[ዓለም] ብዙ ውጊያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም፣ ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16223/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram