avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
26.06.2025 21:31
ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና ዳግም ሊሰጥ ነው 

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የዳግም ብቃት ምዘና መስጠት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ። ምዘናውን ተከትሎ የሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩ የጨመረውን የትራፊክ አደጋ በመቀነስ ረገድ “መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል” የሚል እምነት እንዳለው ሚኒስቴሩ ገልጿል። 

ይህ የተገለጸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 19፤ 2017 ባቀረበበት ወቅት ነው። ሪፖርቱን ለፓርላማው በንባብ ያቀረቡት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ፤ ዳግም ምዘና መስጠት ያስፈለገው የአሽከርካሪነት ስራ “አደጋን ተከላክሎ ከማሽከርከር እና የመንገድ ደህንነትን በላቀ ደረጃ ከማስጠበቅ አኳያ ያለበትን ደረጃ” እንደገና ለማረጋገጥ በማስፈለጉ እንደሆነ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።

ይህንን በጋር ለመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙን ገልጸዋል። በሚኒስቴሩ በተቋቋመ ቡድን አማካኝነት ጥናት ከተካሄደ በኋላ የስራ ደረጃ፤ ስርዓተ ትምህርት እና የስልጠና ማኑዋል መዘጋጀቱን ተናግረዋል። 

“የአሽከርካሪነት ስራ occupational standard እንደሌለው ያወቅነው፤ ይህን ስራ ለመስራት ስንገባበት ነው” ያሉት ዶ/ር አለሙ፤ በአሁኑ ወቅት ለስራው የሚያስፈልግ 40 ሞጁል ስታንዳርድ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16192/

@EthiopiaInsiderNews
22
👏 2
7 13K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram