avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
19.03.2026 11:09
ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አማካሪ እና ሁለት እህት ኩባንያዎቹ፤ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚከናወኑ ስራዎች ለ21 ወራት እንዳይሳተፉ ታገዱ።

ኩባንያዎቹ የታገዱት “በምስራቅ አፍሪካ የኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት” ውስጥ ፈጽመዋቸዋል በተባሉ “የመመሳጠር” እና “የማጭበርበር” ድርጊቶች ምክንያት ነው።

የምስራቅ አፍሪካ የኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት፤ ከወላይታ ሶዶ እስከ ኬንያዋ ሱስዋ ከተማ ድረስ የተዘረጋ 1,045 ኪሎሜትር የሚሸፍን የኃይል ማስተላለፊያን የያዘ ነው።

በኬንያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት መጠንን ለማሳደግ እና ዋጋውን ለመቀነስ የተነደፈው ይህ ፕሮጀክት፤ ኢትዮጵያን ወደ ጎረቤቷ ከምትልከው ኤሌክትሪክ ገቢ እንድታገኝ ያደረጋት ነው።

በዓለም ባንክ፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በፈረንሳይ የልማት ፋይናንስ ተቋም (AFD) ድጋፍ የተገነባው ይህ ፕሮጀክት፤ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ወጥቶበታል።

በዚህ ፕሮጀክት የእቅድ ስራ ላይ ዋና መሥሪያ ቤቱን በለንደን ያደረገው “ፕራይስ ዋተር ሀውስ ኩፐርስ” (PwC) የተሰኘው እውቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ተሳትፏል።

የኦዲት እና ማማከር ሥራዎችን በማከናወን በዓለም ሥመ ጥር ከሆኑ የዘርፉ ተቋማት አንዱ PwC በፕሮጀክቱ የተሳተፈው፤ በአፍሪካ ባቋቋማቸው ተቀጥላ ኩባንያዎች አማካኝነት ነው።

የዓለም ባንክ ትላንት ረቡዕ መጋቢት 9፤ 2018 ምሽት ባወጣው መግለጫ፤ በተቋሙ ሶስት ተቀጥላ ኩባንያዎች ላይ የእገዳ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17680/

@EthiopiaInsiderNews
10
8 6.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram