avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
19.03.2026 03:24
ለንግድ ስራዎች እና ለቱሪዝም ወደ አሜሪካ የሚገቡ ዜጎቻቸው 15 ሺህ ዶላር ዋስትና እንዲያስዙ ከሚገደዱ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ተካተተች።

ዋስትና የማስያዝ አሰራሩ ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በ11 ሀገራት ዜጎች ላይ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

የአሜሪካ መንግስት “ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በህገ ወጥ መንገድ በሀገሩ የሚቆዩ ሰዎችን ለመከላከል” በሚል ምክንያት ዋስትና የማስያዝ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው ካለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጀምሮ ነው።

ይህ አሰራር ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ከተደረገባቸው 38 ሀገራት መካከል ሃያ ሶስቱ አፍሪካውያን ናቸው። ከእነዚህ ሀገራት መካከል የኢትዮጵያ ጎረቤት ጅቡቲ፣ የምስራቅ አፍሪካዎቹ ኡጋንዳ እና ታንዛንያ ይገኙበታል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 9፤ 2018 ይፋ ያደረገው የሀገራት ዝርዝር፤ ዋስትና የማስያዙ አሰራር ተግባራዊ የሚደረግባቸው የአፍሪካ ሀገራትን ቁጥር 29 አድርሶታል።

በዛሬው ዝርዝር ከተካተቱ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ዜጎቿ ለንግድ እና ለቱሪስት ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት 2.3 ሚሊዮን ብር ገደማ ዋስትና እንዲያስዙ ይገደዳሉ።

15 ሺህ ዶላር አስይዘው “ቢ 1” እና “ቢ 2” በመባል የሚጠሩትን የአሜሪካ ቪዛዎች ያገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ጉዟቸውን አጠናቀቅው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ያስያዙት ገንዘብ “ተመላሽ ይደረግላቸዋል” ተብሏል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17669/

@EthiopiaInsiderNews
11
👎 2
11 6.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram