የትምህርት ተቋማት ድንጋጌዎችን ተላልፈው ሲገኙ፤ ከወርሃዊ ገቢያቸው 35 በመቶውን “ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ” የሚያስገድድ ደንብ ተዘጋጀ
አግባብነት ባለው አካል “ተገምግሞ ፈቃድ ያልተሰጠው” መጽሐፍ “ለተማሪዎች ሲሸጡ” ወይም “ሲጠቀሙ” የተገኙ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የትምህርት ተቋማት፤ ከአጠቃላይ ወርሃዊ ገቢያቸው 35 በመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ደንብ ተዘጋጀ።
ተቋማቱ የከተማይቱ የትምህርት ቢሮ ካስቀመጠው አሰራር ውጪ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጡ ከተገኙም፤ ከወርሃዊ ገቢያቸው ተመሳሳይ መጠን ያለው ገንዘብ ለመንግስት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
“ለአንድ ጊዜ ብቻ” ተግባራዊ የሚደረገው ይህ የቅጣት ገንዘብ የተደነገገው፤ “የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር አሰራርና ተጠያቂነት ለማስፈን” በተዘጋጀ ደንብ ላይ ነው።
ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 9፤ 2018 ይፋ የተደረገው ይህ ደንብ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዘጋጀ ነው።
ደንቡ የተዘጋጀው በትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም በሙያ ብቃት ዘርፍ “ይስተዋላሉ” የተባሉ የአሰራር ስርዓት “ክፍተቶችን” “በህግ ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ” እንደሆነ ተገልጿል።
በ2015 ዓ.ም ከጸደቀው ሀገር አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እንዲሁም ባለፈው አመት ጸድቆ ስራ ላይ ከዋለው ከአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር ጋር “የተጣጣመ አሰራርና እና የተጠያቂነት ስርዓት መፍጠር”፤ ሌላው ለደንቡ መዘጋጀት በምክንያትነት የተጠቀሰ ጉዳይ ነው።
በአምስት ክፍሎች እና በ20 አንቀጾች የተከፋፈለው ደንብ፤ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተጠያቂነት ዝርዝር ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17666/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram