avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
12.03.2026 21:38
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት ናዳ አደጋ በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ባጡበት የጋጮ ባባ ወረዳ፤ ከአንድ ቤት እስከ “አምስት ሰዎች” መሞታቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በአደጋው ከሞቱት ውስጥ እስካሁን ድረስ የ70 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

በጋሞ ዞን ባለፈው ሰኞ የካቲት 30 ምሽት እና በማግስቱ መጋቢት 1 “ከባድ ዝናብ” መጣሉን ተከትሎ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ፤ በአራት ወረዳዎች “ከፍተኛ ጉዳት” አድርሷል። አደጋው ከተከሰተባቸው ወረዳዎች መካከል፤ ከፍተኛው የሰዎች ሞት እና ጉዳት የተመዘገበው በጋጮ ባባ ወረዳ ነው።

በወረዳው ማዞ ዶይሳ እና ላካ በተባሉ ቀበሌዎች በደረሰ የመሬት ናዳ ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብሩክ ቡጻ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በአደጋው እስካሁን የደረሱበት ካልታወቁ ሰዎች መካከል እስከ ዛሬ ሐሙስ ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ የ58 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

“ከአንድ ቤተሰብ አራትም፣ ሶስትም፤ ሁለትም፣ አምስትም የሞተ አለ” ያሉት አቶ ብሩክ፤ ከአንድ ግለሰብ በስተቀር በአደጋው ሰለባ የሆኑት ሁሉም የማዞ ዶይሳ ቀበሌ ነዋሪዎች እንደነበሩ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።

በአደጋው ደብዛቸው የጠፋ 62 ሰዎችን የማፈላለግ ስራ አሁንም መቀጠሉን የተናገሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፤ የሟቾች አስከሬን ተቆፍሮ የወጣው በአካባቢው ማህበረሰብ ትብብር እንደሆነ አብራርተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17658/

@EthiopiaInsiderNews
😭 6
4
💔 3
3 8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram