avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.03.2026 17:50
በፌዴራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር የአዋጅ ረቂቅ ላይ የስፖርት ውርርድን በተመለከተ የሰፈረው ድንጋጌ፤ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ስልጣን ጋር “ግጭት የሚፈጥር ነው” የሚል ጥያቄ አስነሳ።

ድንጋጌው የሀገሪቱ የስፖርት ልማት ከስፖርት ውርርድ በሚገኝ ገቢ እንዴት መደጎም እንዳለበት የሚያመለክት እንጂ፤ የሌሎች መስሪያ ቤቶችን ስልጣን የማይቃረን እንደሆነ ምላሽ ተሰጥቷል።

ይህ ምላሽ የተሰጠው፤ የአዋጅ ረቂቁን በተመለከተ ትላንት አርብ የካቲት 27፤ 2018 በፓርላማ በተካሄደ የህዝብ ውይይት መድረክ ላይ ነው።

በውይይቱ ላይ ጥያቄ ከተነሳባቸው የረቂቅ አዋጁ ድንጋጌዎች መካከል “የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ በሀገሪቱ ውስጥ ስለሚተዳደርበት ስርዓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል” የሚለው አንዱ ነው።

በዚህ ድንጋጌ ላይ ጥያቄ ያነሱት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ት ቤዛ ግርማ፤ የስፖርት ውርርድን ጨምሮ ሎተሪ ወይም የእድል ጨዋታ ስራ ፈቃድ የመስጠት፣ የመሰረዝ፣ የመቆጣጠር፣ የሎተሪ ጨዋታዎችን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ የመሳሪያ አይነቶችን የመወሰን፣ ወደ ሀገር እንዲገቡ ፍቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ለገቢዎች ሚኒስቴር እንደሆነ አስታውሰዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ “ዝርዝር ህግ እስኪወጣ ድረስ” እነዚህን ስራዎች እንዲያከናውን ስልጣኑን “በውክልና” የሰጠው ለኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደሆነም ገልጸዋል። በአዋጅ ረቂቁ ላይ ይህ ስራ ለባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መሰጠቱ፤ “አንድን ስራ ለሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መስጠት” እንደሆነ ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17639/

@EthiopiaInsiderNews
12
6 8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram