avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
06.03.2026 12:07
በኦሮሚያ ክልል ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ግጭት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፤ “የጦር ወንጀሎች” ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸሙን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

ሰራዊቱ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ “በቡድን አስገድዶ መድፈር” የደረሰ ጾታዊ ጥቃት፣ “የወሲብ ባርነት”፣ “ከህግ ውጭ ግድያ”፤ “ስቅየት” እና “የሲቪል ንብረት ውድመት” መፈጸሙን ድርጅቱ ገልጿል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህን ያስታወቀው፤ ዛሬ አርብ የካቲት 27፤ 2018 ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርት ነው።

የምርመራ ሪፖርቱ በኦሮሚያ ክልል፣ በቄለም ወለጋ ዞን፣ ሳዮ እና አንፊሎ ወረዳዎች፤ በሰላማዊ ሰዎች በተለይም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የኦነሰ ታጣቂዎች ፈጽመዋቸዋል የተባሉትን “የጭካኔ ድርጊቶች” የሰነደ ነው።

የሰራዊቱ ታጣቂዎች “የጭካኔ ድርጊቶቹን” የፈጸሙት ከ2012 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት እንደሆነ የአምነስቲ የምርመራ ሪፖርት ያመለክታል።

ኦነሰ ከመከላከያ ሰራዊት እና በአጋርነት ከተሰለፉ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር እያደረገ ያለው ውጊያ የተጀመረው በ2011 ዓ.ም ነው።

በአራት ዓመት ውስጥ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ብቻ ላካተተው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ሪፖርት፤ የቡድን አስገድዶ መድፈር የደረሰባቸው 10 ሰለባዎች ቃለ መጠይቅ እንደተደረገላቸው ድርጅቱ ገልጿል።

በምርመራው ወቅት የጤና ባለሙያዎች ምስክርነቶች መቀበሉን እና የተጎጂዎቹን የህክምና መዝገቦች መፈተሹን አምነስቲ አስታውቋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17629/

@EthiopiaInsiderNews
😢 10
6
👍 3
11 8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram