avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
02.03.2026 22:12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ የሚገኙ ተቋማት ለድጋፍ የሚሰበስቡትን ገንዘብ፤ ለዚሁ ተግባር በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ውስጥ በ24 ሰዓት ውስጥ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ አዲስ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጀ።

ከህዝብ፣ ከመንግስት እና ከበጎ አድራጎት ለጋሾች የሚሰበሰበው ይህን መሰሉ ሀብት መመዝገብ ያለበት፤ የከተማ አስተዳደሩ በሚከተለው የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት መሠረት እንደሆነም መመሪያው ያዝዛል።

“የድጋፍ ሀብት አሰባበሰብ እና አስተዳደር አፈጻጸም” የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ረቂቅ መመሪያ የተዘጋጀው ባለፈው ጥር ወር ነው።

በሶስት ክፍሎች እና 15 አንቀጾች የተከፋፈለው መመሪያው፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በድጋፍ ሀብት ምንጭ አሰባሰብ ላይ ያለውን ስልጣን፣ የአስተዳደር ሥርዓት እና የድጋፍ ሀብት የሚሰበሰብባቸውን ምንጮች የዘረዘረ ነው።

በመመሪያው መሰረት “የድጋፍ ሀብት ምንጮች” ተብለው የተዘረዘሩት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ግለሰቦች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ናቸው።

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ የበጀት ድጋፍ እንዲሁም ከሌሎች ህጋዊ ምንጮች የሚገኝ ድጋፍም፤ በሀብት ምንጭ ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ክፍል ኃላፊ አቶ አብይ ቢተው፤ ተቋማት እስካሁን የድጋፍ ሀብቶችን ሲሰበስቡ የቆዩት “በተበጣጠሰ መንገድ” እንደሆነ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የተወሰኑ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ይህን በተመለከተ የየራሳቸው መመሪያ እንዳላቸው አቶ አብይ ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17621/}

@EthiopiaInsiderNews
11
😢 2
👍 1
👎 1
😁 1
💔 1
13 10.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram