avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
28.02.2026 18:35
በኳታር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና መቀመጫውን በባሕሬን ዋና ከተማ ማናማ ያደረገው ቆንስላ በየሀገራቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የደህንነት ማስጠንቀቂያ ሰጡ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው “የጸጥታ ሁኔታ” ምክንያት የተወሰኑ በረራዎቹን እንደሰረዘ ይፋ አድርጓል።

የበረራ ስረዛው የተደረገው እና የደህንነት ማስጠንቀቂያው የተሰራጨው፤ እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 21፤ 2018 ረፋድ ጀምሮ በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከጀመሩ በኋላ ነው።

ኢራን በሁለቱ ሀገራት ለተፈጸመባት ጥቃት፤ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ወዳሉባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ሚሳኤሎችን በመተኮስ አጸፋውን መልሳለች።

በኢራን ኢላማ ከተደረጉ ሀገራት አንዷ በሆነችው ባህሬን የምትኖር አንዲት ኢትዮጵያዊት፤ “ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ” መስማቷን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጻለች። ጥቃት ስለተፈጸመበት ቦታ የምታውቀው ነገር እንደሌለ የተናገረችው በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኘው ይህቺው ኢትዮጵያዊት፤ በሁኔታው ፍርሃት እንዳደረባት አስረድታለች።

በባህሬን መዲና ምስራቃዊ ክፍል የምትኖረው ሁለተኛዋ ኢትዮጵያዊትም፤ ዛሬ ረፋድ ላይ የፍንዳታ ድምጽ መስሟቷን አረጋግጣለች። በከተማው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የደህንነት ስጋት እንዳለም ገልጻለች።

በማናማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽህፈት ቤትም፤ ዛሬ ከሰዓት በፌስቡክ ገጹ “አስቸኳይ የደህንነት መመሪያ” በሀገሪቱ ላሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሰራጭቷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17596/
12
😁 2
8 9.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram